Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

6 ሺህ 142 ኩንታል ስኳርና ጨው በህገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ 6 ሺህ 142 ኩንታል ስኳርና በአዮዲን ያልታከመ ጨው መያዙ ተገለፀ፡፡
የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰይድ ይማም እንደገለጹት÷ ስኳር እና ጨዉ የተያዘው ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በወረዳው የህገወጥ ቁጥጥርና ኮንትሮባንድ ግብረ ሃይል እና በገበያ ማረጋጋት ግብረ ሀይል በቦታው በመገኘት በቅንጅት በተደረገ የመጋዘን ፍተሻ ነው።
በዚህም 4 ሺህ 26 ኩንታል ስኳር፣ 1 ሺህ 600 ኩንታል በአዮዲን ያልታከመ ጨውና በአዮዲን የታከመ 516 ኩንታል ጨው በህገ ወጥ መንገድ በተለያዩ መጋዘኖች ተከማችቶ መገኘቱን ከወረዳው ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version