አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሃላላ ኬላ ተነግሮ የማይጠገብ ታሪክ ያለው ስፍራ mሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገበታ ለሃገር መረሃ-ግብር የኮይሻ ፕሮጀክትን የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታን ለማስጀመር በዳውሮ ዞን በመገኘት ንግግር አድርገዋል፡፡
እኛ የምንቀናባቸው ብዙዎቹ የውጭ ሃገራት ሜዳና አሸዋማ ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኮይሻን ጨምሮ በዳውሮ ዞን ያሉ ተፈጥራዊ የቱሪስት መዳረሻዎችን አካባቢያዊ በረከቶች በመሆናቸው ያላቸውን ታሪክ በሚመጥን መልኩ በሚገባ አልምቶ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በዞኑ በተለያዩ ክላስተሮች ተከፋፍሎ እንደየአካባቢው ፀጋ እንዲለማ ለታቀደው ፕሮጀክቱም በቂ ዝግጅት የተደረገ መሆኑን ዛሬ በማስጀመሪያ መረሃ-ግብሩ አመላክተዋል፡፡
እንደ አባቶቻችን በጉዟችን የጀመርነውን ሁሉ የምናጠናቅቅ መሆናችን አይቀርም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህንንም ፕሮጀክት ከአንድ አመት ባነሰ ጊዜ አጠናቀን እንመርቃለን ብለዋል፡፡
ለዚህም የክልሉ መንግሥትና ሌሎች የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች ተገቢውን የአፈፃፀም ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
በሶዶ ለማ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

