አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የድሬደዋ ብልፅግና ፓርቲ የፓርቲውን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት እና ማኒፌስቶ ይፋ አደረገ።
“ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በመጪው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፈው ፓርቲው ለአባላቱ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቱን እና ማኒፌስቶውን አስተዋውቋል።
በመድረኩ ላይ የድሬደዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋርን ጨምሮ የአስተዳደሩ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፈጡም መሀመድና የፖርቲው አባላት ተገኝተዋል።
ፖርቲያችን የሀገራችንን ፖለቲካ የለወጠ ነዉ ያሉት የድሬደዋ ብልፅግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ የብልግና ፓርቲ ሠላም የሰፈነባትና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚሠራ ፓርቲ ነው ብለዋል።
ለዚህም አተገባበር ይረዳ ዘንድ ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና የህዝብ ይሁንታን በማግኘት ይጠናቀቅ ዘንድ ብልፅግና ከአባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር በመተባበር እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
የአምፖል ብርሃን ባለበት ጨለማ አይነግስም ያሉት የድሬዳዋ ብልፅግና ፖርቲ ሃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ የብልፅግና ማኒፌስቶ ድርሰት ሳይሆን የህዝብና የፖርቲው መግባቢያ የቃል ኪዳን ሰነድ ነው ብለዋል።
የድሬደዋ ብልፅግና ፖርቲ የሚወዳደርበትን የሚበራ የአምፖል ምልክት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋርና የድሬዳዋ ብልፅግና ፖርቲ ሃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ በጋራ ለፖርቲው አባላት ይፋ አድርገዋል።
የብልፅግና ፖርቲ በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ስር ከመቶ በላይ እጩ ተወዳዳሪዎችን ያቀረበ መሆኑን የተናገሩት አቶ መብራቴ ገብረየስ ከእነዚህም መካከል ከ50 በመቶ በላዩ ወጣት በመሆናቸው ፖርቲው የመጪው ትውልድ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

