አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ለ3 ሚሊየን 165 ሺህ ዜጎች እርዳታ መከፋፈሉን የፌዴራል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል የተካሄደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በተፈጠረ ሰብዓዊ ቀውስ ለበርካታ ወገኖች ድጋፉ ተደርጓል ብለዋል።
በአካባቢው የነበረው ችግር ከባድ ቢሆንም ሰብዓዊ ድጋፉ ላይ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግና ኮሚሽኑም ጠንካራ ሥራ በመሥራቱ እርዳታው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ለዜጎች ምግብ ነክ አቅርቦቶችን ማቅረብ መቻሉን አስታውቀዋል።
ከመንግሥት ድጋፍ ጎን ለጎን 10 የሚጠጉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም በአካባቢው ላይ የሚታየውን ሰብዓዊ ችግር ለመፍታት ከፍተኛ የሆነ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ አቶ ምትኩ ጠቁመዋል።
ድጋፉ በመቐለ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል የፌደራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተወካዮች፣ የክልል ሴክተር ቢሮዎች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካዮች እና ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችን ያቀፈ በመሆኑ ለችግሩ ሰፋ ያለ ምላሽ እንዲሰጥ አስችሏል ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!