አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በአዲስ አበባ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ከመጣው የኮቪድ ህሙማን ቁጥር ጋር በታያያዘ ከአዲስ አበባና ከብሔራዊ ድንገተኛ ምላሽ አስተባባሪ ቡድኖች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት የህክምና አቅምን ከማጎልበት አንፃር ሁሉም ሆስፒታሎች ከመሰረታዊ የጤና አገልግሎት በተጨማሪ የኮቪድ ህክምናን ጎን ለጎን እንዲሰጡ ማስቻል እንደሚገባ ተነስቷል።
ከዚህ ባለፈም ራስን በቤት ውስጥ ለይቶ በማቆየት ሂደት ውስጥ የህሙማን ክትትልንና የአምቡላንስ አገልግሎትን ማጠናከር ይገባልም ተብሏል።
እንዲሁም በኮቪድ ህክምና ስራው ላይ የግል ሆስፒታሎች በበቂ ሁኔታ እንዲሳተፉ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!