Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአዲስ አበባ የአካባቢ ብክለት መረጃን መሠብሠብ የሚያስችል ሶፍትዌር ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን ለመዲናዋ የአካባቢ ብክለት መረጃን መሠብሠብ የሚያስችለውን ሶፍት ዌር ስራ አስጀመረ።

ኮሚሽኑ በከተማዋ እየጨመረ የመጣውን የአካባቢ ብክለት ለመቆጣጠር ከ500 በላይ በሙያው የተመረቁ ወጣቶችን በማህበር አደራጅቶ ወደ ስራ ማስገባቱ ይታወሳል፡፡

ማህበራቱ በወረቀት ሲሰሩት የነበረው የመረጃ አሰባሰብ ጊዜ እና ሀብትን ለብክነት የሚዳርግ አሠራር በመሆኑ አዲስ መተግበሪያ አስገንብቶ ወደ ስራ መግባቱን የኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙክታር ሰኢድ ተናግረዋል።

መረጃ መሠብሰቢያ ሶፍትዌሩ የብክለት ተቆጣጣሪ ባለሙያዋቹ ያስገቡለትን መረጃ የመተንተን፣ ለይቶ የማስቀመጥ፣ በካይ ድርጅትና ግለሰቦችን እንዲሁም የብክለቱን ምንጭ የመለየት ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለተቋሙ ከፍተኛ ባለሙያዋች እና ለከተማዋ ሀላፊዋች ለውሳኔ አመቺ መረጃዎችን ያቀርባልም ነው የተባለው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version