Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተተኳሽ ጥይቶች ሲገበያዩ የተገኙ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ 2 ሺህ ተተኳሽ የክላሽንኮቭ ጥይቶችን በድብቅ ሲገበያዩ የተገኙ ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የታክቲክ ወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ኮማንደር አሊ ሰይድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ጥይቶቹን በከተማው ቀበሌ ሶሰት አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በድብቅ ሲገበያዩ እጅ ከፍንጅ ተደርሶባቸው ነው።

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረትም ሻጭ፣ ደላላ እና ገዥ በቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አስረድተዋል።

አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ተገቢውን ህጋዊ ቅጣት እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል።

ህብረተሰቡ ለሀገር አንድነትና ሰላም ሲባል ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን በመሆን ህገ ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version