አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር በጅማ ከተማ የታክስ ስወራ እና ማጭበርበር በሃገር ላይ እያደረሰ ባለው ጉዳት ዙሪያ ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡
ውይይቱ ‘ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለሁለተናዊ ገቢ አሰባሰብ’ በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው፡፡
ሰላም፣ ልማት እና የሃገር ደህንነት ከገቢ ዉጭ ሊታሰብ አይችልም ያሉት የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዘመዴ ተፈራ ናቸው።
ሚኒስትር ዴኤታው በመድረኩ፤ ጠንካራ መንግስት መፍጠር የሚቻለው ፣ የሃገር ደህንነትን ለማስጠበቅ እንዲሁም ከውጭ ሃይሎች ድጋፍ ጥገኝነት ለመላቀቅ ኢኮኖሚ ከሚያመነጨው ገቢ ግብር መሰብሰብ ሲቻል ነው ብለዋል።
የጅማ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ደሜ ከበደ፤ የመንግስት መስሪያቤቶች እና ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት መካከል ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር ባለመኖሩ በታክስ አሰባሰብ ላይ ክፍተት መፈጠሩን ጠቅሰዋል።
በመድረኩ የታክስ ስወራ እና ማጭበርበር እያደረሰ ያለው ጉዳት እና የደረሰኝ አጠቃቀም ላይ ትኩረት ያደረጉ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነዉ።
በውይይቱ ከጅማ ከፋ እና ሸካ ዞኖች እንዲሁም የጅማ ቦንጋ ሸካ አጋሮ እና ከሊሙ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በአልማዝ መኮንን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

