Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዓድዋ ድል እውነተኛ ታሪክ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ከምሁራን ብዙ ይጠበቃል – ዶክተር ሒሩት ካሳው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአድዋ ድል እውነተኛ ታሪክ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ከምሁራን ብዙ እንደሚጠበቅ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሒሩት ካሳው ተናገሩ።

ባለፉት ዓመታት የተዛባውን ታሪክ ለማስተካከል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ብዙ መስራት እንዳለባቸውም አመላክተዋል።

125ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በማስመልከት “ዓድዋ በታሪክ ምሁራን ዕይታ” በሚል መሪ ሃሳብ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

ሚኒስትሯ በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር የአድዋ ድል እውነተኛ ታሪክ ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ከምሁራን ብዙ መስራት ይጠበቃል።

ምሁራን በአድዋ ድል ላይ የተለያዩ ጥናቶችን አካሂደው ለታሪክ እንዲቀመጡ በማድረግ ከነበረው በተጨማሪ መስራት ይኖርባቸዋልም ብለዋል።

የአድዋ ድል ታሪክ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሁን ካለበት የበለጠ እንዲታወቅ ምሁራን ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው አውስተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version