Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

125ኛው የአድዋ ድል በዓል በጎንደር ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአድዋ ድል በዓል በጎንደር በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

በበዓሉ አባት አርበኞች፣ ወጣቶች፣ ልዩ ልዩ የጸጥታ አባላትና ከተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የተወጣጡ ነዋሪዎች ታድመውበታል።

መነሻውን አርበኞች አደባባይ አድርጎ በጃንተከል መስቀል አደባባይ በመከበር ላይ የሚገኘው በዓሉ የጀግኖች አርበኞች የአድዋ ዘማቾችን ገድል የሚዘክሩ ትርዒቶችና ጭፈራዎችም እንደቀረቡበት አብመድ ዘግቧል።

ጎራዴ፣ ጋሻና ጦር የያዙ አርበኞች፣ ፉከራና ቀረርቶ የሚያወርዱ ወጣቶች፣ የአባቶችን ገድል ለመዘከር የታደሙ ፈረሰኞች የበዓሉ ድምቀት ሆነዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version