Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የልዩ ዘመቻዎች ኃይል የአየር ወለድ ስልጠና ማጠናቀቂያ የአየር ወለድ ዝላይ ትርኢት በዱከም አካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የልዩ ዘመቻዎች ኃይል የአየር ወለድ ስልጠና ማጠናቀቂያ የአየር ወለድ ዝላይ ትርኢት በዱከም አካሄደ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ከፍተኛ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች በተገኙበት በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ የአየር ወለድ ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሐግብር በዱከም የአየር ወለድ ዝላይ ሜዳ ላይ አካሂዷል።

የዝላይ ትርኢቱ የልዩ ዘመቻዎች ኃይል አየር ወለድ የደረሰበትን ከፍተኛ አቅም የሚያሳይ መሆኑንና ሰልጣኞቹ ከአየር ወለድ ስልጠናው በተጨማሪ ልዩ ልዩ የኦፕሬሽናልና የውጊያ ስልጠናዎችን የወሰዱ መሆናቸው መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

በሌላ በኩል በልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ስር የሚገኘውን የአየር ወለድ ትምህርት ቤትን ለማጠናከር የአዲስ ህንጻ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ ይቀመጣል ተብሏል።

በቢሾፍቱ የአየር ወለድ ትምህርት ቤት ግቢ አጠቃላይ የአየር ወለድ የስልጠና ሂደት ጉብኝትና የመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጥ መርሃግብሩ እንደሚሄድ ነው የተገለጸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version