አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገ ወጥ መልኩ ሲዘዋወሩ የነበሩ 380 የክላሽንኮቭ ተተኳሽ ጥይቶች ተይዘዋል።
ተተኳሽ ጥይቶቹ የተያዙት ከቆቦ ከተማ ወደ ሀራ ከተማ ሲጓጓዝ ልዩ ስሙ አልዋ በተባለ ቦታ በአካባቢው ሚሊሻ አባላት በተደረገ ክትትል ነው።
ከዚህ ጋር በተያያዘም ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ማጣራት እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡
የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በቀጠናው ያለውን የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ እና የህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዝውውር የመቆጣጠር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
በዚህ ሥራ ለተሳተፉ የአካባቢው የሚሊሻ አባላት ምስጋና በማቅረብ ህብረተሰቡም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ትብብራቸውን እንዲቀጥሉ ጽህፈት ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በይክበር አለሙ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

