Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሰቆጣ ቃል-ኪዳን ስምምነት መሠረት ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ወረዳ በሰቆጣ ቃል-ኪዳን ስምምነት መሠረት ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ተመረቀ፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ሃይለ ማርያምን ጨምሮ የክልልና የዞን አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በሰቆጣ ቃል ኪዳን የተገነባው የመስኖ ካናል ፕሮጀክት ከ80 ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ይችላል ተብሏል፡፡

እስካሁንም 43 ሄክታር እያለማ እንደሚገኝ ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version