Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኦሞቲክ የተሰኘ ማህበር በ114 ሚሊየን ብር በኮይሻ ሎጅ ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሞቲክ ጠቅላላ ንግድ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ114 ሚሊየን ብር ደረጃውን የጠበቀ ሎጅ በኮይሻ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የማህበሩ የሎጆችና ሆቴሎች መምሪያ ሃላፊ አቶ አብዲ ፤ ማህበሩ በገበታ ለሀገር በታቀፈው የኮይሻ ፕሮጀክት ለሚገነባው ሎጅ አምስት  ሄክታር መሬት ተረክቧል ብለዋል።

በሶስት ምዕራፍ ለሚካሄደው ግንባታ 114 ሚሊየን ብር በጀት መመደቡንና በአሁኑ ወቅት ግንባታውን ለማስጀመር በዝግጅት ላይ  እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የእንግዳ ማረፊያ ናሌሎች አገልግሎት መስጫ ተቋማትን የያዘው የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ በተያዘው ዓመት ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ  መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኮይሻ የጨበራ ጩርጩራ ፓርክን ጨምሮ በርካታ የተፈጥሮ መስህቦች ያሉት አካባቢ በመሆኑ በተፈጥሮ ሀብቱ ላይ ጉዳት በማያደርስ መስኩ ግንባታው እንደሚከናወን አቶ አብዲ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ከ400 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ ዕድል መፍጠራቸውን ጠቁመው በቀጣይ የስራ ዕድል የሚፈጠርላቸው ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ሊጨምር ይችላል ነው ያሉት።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version