አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የአማራ እና ደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች አስታውቀዋል፡:
ምርጫውን ጨምሮ ሌሎች የፀጥታ ችግሮችን መከላከል እና መቆጣጠር የሚያስችሉ አደረጃጀቶችን እስከ ቀበሌ ድረስ በማቋቋም ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የየክልሎቹ ፖሊስ ኮሚሽነሮቹ የምርጫው ሂደት ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ለዚህም ለሁሉም የጸጥታ አካላት አደረጃጀቶች አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ስራ ተገብቷል ነው ያሉት፡፡
በምርጫ ሂደቱ ችግሮች ቢፈጠር በአፋጣኝ መፍታት የሚስችል እስከ ቀበሌ የሚደርስ አደረጃጀት መዋቀሩንም አብራርተዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ተጨባጭ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ እያንዳንዱ አካባቢ ላይ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ለፖሊስ አባላት መመሪያ መሰጠቱንም አስረድተዋል፡፡
ስለ ምርጫ ስነ ምግባርም ለሁሉም የፖሊስ አባላት ስልጠና መሰጠቱንም ነው የተናገሩት፡፡
ማንኛውም ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ያለምንም እንከን እንዲንቀሳቀስ በቅንጅት እንደሚሰራ ያነሱት ኮሚሽነሮቹ፥ ፓርቲዎችም ዜጎችን ለአላስፈላጊ ግጭት ከሚዳርጉ ድርጊቶች መቆጠብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ምርጫው በታቀደው መልኩ ሰላማዊ እና ስኬታም ሆኖ እንዲጠናቀቅም ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጎን በመቆም የሚስተዋሉ አላስፈላጊ ድርጊቶችን ማጋለጥ እንዳለበት ነው የፖሊስ ኮሚሽነሮች ያሳሰቡት፡፡
ለዚህም በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ቅሬታዎችን በመቀበል አፋጣጥ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

