Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ከዘርፉ ከ17 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘትም ማቀዱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ከዘርፉ ከ17 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘትም ማቀዱን አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ይህንን ያለው ከተቋሙ፣ ከተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ጋር የዘርፉን የሰባት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው፡፡

በዚሁ ወቅት ከባለፈው በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በተሻለ ሁኔታ ከዘርፉ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት መቻሉንም ገልጿል፡፡

በተደረገው ተቋማዊ ሪፎርም ተግባራት በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የማዕድን ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ወይዘሮ ስመኝ ገልጸዋል።

መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት የሠጠው በመሆኑ አመራሩና ሠራተኛው በጋራ ተናቦ በመስራት የተጣለበትን ሃገራዊ ተልዕኮ መወጣት ይጠበቅበታል ብለዋል።

የቀጣይ 5 ወራት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችም ቀርበዋል።

የሲቪል ሠርቪስ ፍኖተ ካርታም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ በህዝብ በሚመረጥ መንግሥት የሚነድፋቸውን የልማት ዕቅዶች ማሳካት የሚችል፣ የህዝብ አገልጋይነትን መንፈስ የተላበሰና ነጻ፣ገለልተኛና ብቃት ያለው የመንግስት አገልግሎት ስርዓት መገንባት የፍኖተ ካርታው ዋናው ዓላማ መሆኑንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/…/www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version