አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛውን አጠቃላይ ምርጫ ለመታዘብ ማመልከቻ ላስገቡ እና በመጀመሪያ ዙር ላለፉ ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሥልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናው የተለያዩ ክፍሎች ያሉት ሲሆን በቦርዱ የፕሮግራም ባለሙያ-የውጭ ግንኙነት ክፍል፣ በቦርዱ የሥርዓተ -ፆታ እና አካታችነት ክፍል እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ ተሞክሮ ባላቸው ባለሙያዎች ቀርቧል።
የቦርድ አመራር ብዙወርቅ ከተተ ሥልጠናው የተወሰኑ የ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ያስገቡት ሠነድ ላይ የዕቅድ አወጣጥና ዘዴ ክፍተት በመታየቱ መስጠት እንዳስፈለገ ተናግረዋል።
ለምን ምርጫ መታዘብ ያስፈልጋል፣ የምርጫ መታዘብ ዕሴቶችና ጥቅሞች፣ በምርጫ መታዘብ ወቅት የሚጠበቁ የሥነ-ምግባር ደንቦችና ኃላፊነቶች፣ አካታችነትን ያማከለ የምርጫ መታዘብ ሂደት የሚሉት ደግሞ የስልጠናው አጀንዳዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡
እንዲሁም የምርጫ መታዘብ አቀራረብ ዘዴ ዓለም ዐቀፍ ተሞክሮዎች፤ ማለትም የምርጫ መታዘብ ስልት፣ ሪፖርቶችን ማደራጀት፣ የአካታችነት መርሆችን ተግባራዊ ማድረግ የሚሉት እንዲሁ የሥልጠናው ዋና ዋና አጀንዳዎች መሆናቸውን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

