Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፈረንሳይ ከ50 ዓመታት በላይ የሆናቸው የቅኝ ግዛት ዘመን መረጃዎችን ይፋ ልታደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የቅኝ ግዛት ዘመን መረጃዎች ማግኘት የሚቻልበትን ሂደት የሚያቀል ውሳኔ አሳለፉ።

ይፋ የሚደረጉት የቅኝ ግዛት ዘመን መረጃዎች የአልጀሪያ የነፃነት ጦርነትን ጨምሮ ከ50 ዓመታት በላይ የሆናቸው መረጃዎች ናቸው ተብሏል።

በሀገሪቱ ብሄራዊ የመከላከያ ሰራዊት የመሬት ክፍል ላለፉት 50 ዓመታት በሚስጥር ተይዘው የነበሩ መረጃዎች ይፋ እንደሚደረጉ ቢቢሲ በዘገባው ላይ አስፍሯል።

ይህ ለውጥም ተመራማሪዎች በፍጥነት መረጃዎችን እንዲያገኙ ፣ እርቅ ለማውረድ እና  ከፈረንሳይ የአልጀሪያ የቅኝ ግዛት ወርስ ለመላቀቅ ያስችላል ተብሏል።

በቅርቡ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በፈረንሳይ ጦር ስቃይ የደረሰበት እና የተገደለውን የአልጀሪያ የነፃነት ምልክት አሊ አድንቀው ንግግር አድርገው ነበር።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version