Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አንዳንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ጁንታው ያደራጃቸውን ሰዎች ሃሳብ ብቻ በመውሰድ ስለ ትግራይ የተዛባ መረጃ ማውጣታቸው ስህተት ነው – ዶክተር ሙሉ ነጋ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኀን ጁንታው ያደራጃቸውን ሰዎች ሃሳብ ብቻ በመውሰድ ስለ ትግራይ የተዛባ መረጃ ማውጣታቸው ስህተት መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ አስታወቁ።

ዶክተር ሙሉ በሰጡት መግለጫ የተወሰኑ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኀን ስለ ትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ያወጡት መረጃ መሬት ላይ የሌለና የተዛባ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በተጨማሪም የህወሓት ጁንታ ቡድን ያደራጃቸውን ሰዎች ሃሳብ ብቻ በመውሰድ ስለ ክልሉ የተዛባ መረጃ ማውጣታቸው ተገቢነት እንደሌለው ነው ያስረዱት።

የጥፋት ቡድኑ በተለያየ ቦታ ተበትኖ ችግር እየፈጠረ፣ ሕዝቡን እየጎዳና የኅብረተሰቡንም ሠላም ለማወክ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ይህን በሚያደርጉ ላይም ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ብለዋል።

መገናኛ ብዙኀኑ ግን የጥፋት ቡድኑ አባላት የሚያደርሱትን ጉዳት የመንግስት የጸጥታ አካላት እንደፈጸሙ አድርገው መዘገባቸውን ነው የገለጹት።

በክልሉ እየተፈጸሙ ለሚገኙ ችግሮች ዋነኛው ተጠያቂ የህወሓት ቡድን መሆኑንም መግለጻቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

Exit mobile version