አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት የኑሮ ንረቱን ለማቃለል የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ማስገባት እንደቀጠሉ መሆኑ ተገልጿል ፡፡
በዛሬው ዕለትም የአራዳ ክፍለ ከተማ በአስሩም ወረዳዎች ለሚገኙ የሸማች ማህበራት ባገኙት የተዘዋወሪ ብድር የ30 ሚሊየን ብር ወጪ ጤፍን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና እና የኢንዱትሪ ምርቶች በማስገባት ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማከፋፈልዝግጁ መሆናቸው ተመላክቷል።
የሸማቾች የህብረት ስራ ማህበቱም በተተመነላቸው ዝርዝር ዋጋ መሰረት ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያከፋፍሉ ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኑሮ ውድነት ማቃለያ ህብረተሰቡ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርቶችን በሸማቾች ማህበራት በኩል ቀጥታ እንዲያገኙ 500 ሚሊየን ብር ተዘዋዋሪ ብድር እንዲያገኙ መደረጉን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

