አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀሰተኛ ደረሰኝ በማሰራጨት ሲያጭበረብሩ የነበሩ 42 ድርጅቶች መለየታቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ድርጅቶቹ ባለፉት ሰባት ወራት በሃሰተኛ ደረሰኝ ሲያጭበረብሩ የነበሩና በጥናት የተለዩ መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡
ከተዘረዘሩት ህገ ወጥ ድርጅቶች ግብይት የፈፀሙ አካላት ኦዲት እንደሚደረጉ በመጥቀስም፥ ድርጅቶች በቀጣይ ከተዘረዘሩት ድርጅቶች ግብይት እንዳይፈጽሙም መልዕክት አስተላልፏል፡፡
የድርጅቶቹ ድርጊት ሃገር ማግኘት የሚገባትን ገቢ ከመሳጣቱም በላይ የንግድ ስርዓቱን በማዛበት ህጋዊ ነጋዴዎችን ከገበያ እንደሚያስወጡም ገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

