Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአፍሪካ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4ሚሊየንን አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4 ሚሊየን ማለፉን የአህጉሪቱ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታውቋል፡፡

እንደማዕከሉ መረጃ በአህጉሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ4 ሚሊየን 5 ሺህ 200 በላይ ሲሆን ከ107 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በአንጻሩ ከ3 ሚሊየን 589 ሺህ በላይ ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ ግብጽ እና ኢትዮጵያ ቫይረሱ ከጸናባቸው ሃገራት መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡

እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ119 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ ከ2 ሚሊየን 650 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በአንጻሩ ከ96 ሚሊየን 264 ሺህ በላይ ሰዎች አገግመዋል፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን እና ዎርልድ ኦ ሜትር

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version