Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኮሮና ቫይረስ ክትባት በተለያዩ ክልሎች መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ ክትባት በተለያዩ ክልሎች መሰጠት ጀምሯል፡፡

ክትባቱ በተለያዩ ክልሎች መሰጠት የጀመረ ሲሆን፥ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በትግራይ ክልል በመቐለ ከተማ በመገኘት ክትባቱን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

በተመሳሳይ በሶማሌ ክልል ክትባቱ መሰጠት ሲጀምር የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ክትባቱን በመውሰድ አስጀምረዋል፡፡

በአፋር ክልል በዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በደቡብ ክልል ደረጃ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲም ክትባቱ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በተያያዘም በሃረሪ ክልል በጀጎል ሆስፒታል በይፋ መሰጠት ተጀምሯል፡፡

ክትባቱን የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ዓለምፀሃይ ጳውሎስ አስጀምረውታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version