Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን የስደተኞች ተጠባባቂ ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን የስደተኞች ተጠባባቂ ኮሚሽነር ኢብራሂም አብደላ ጋር በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውን ስደተኞችን በተመከለተ መወያየታቸውን ገለጹ።

አምባሳደር ይበልጣል ከኮሚሽነሩ ጋር በነበራቸው ቆይታ በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወቅታዊ ሁኔታ ምን እንደሚመስልና እየተካሄዱ ያሉ የድጋፍ ስራዎችን በተመለከተ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሱዳን የሚገኙ ዜጎች በፈቃደኝነት ወደ ሃገራቸው በሚመለሱብት ሁኔታ ዙሪያ መወያየታቸውንም ነው አምባሳደሩ የገለጹት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version