Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሩሲያ በ2020 የአሜሪካ ምርጫ ለዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የቅስቀሳ ዘመቻ ድጋፍ ስታደርግ ነበር – የአሜሪካ የመረጃ ሃላፊዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በ2020 የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ እንዲያሸንፉ ለደጋፊዎቻቸው የቅስቀሳ ዘመቻ ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበር የአሜሪካ መረጃ ሃላፊዎች ገለፁ።

ሩሲያ የ2020 የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ በሆኑት ጆ ባይደን ላይ አሳሳች እና ያልተረጋገጡ ክሶችን ስታሰራጭ እንደነበር ነው የአሜሪካ መንግስት ሪፖርት ያመላከተው።

ሆኖም ሩሲያ በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጣልቃ ገብታለች ተብሎ የሚቀርብባትን ክስ ውድቅ ስታደርግ ቆይታለች።

ባለ 15 ገፁን ሪፖርት የአሜሪካ ብሄራዊ የመረጃ ዳይሬክቶሬት የለቀቀው ሲሆን ሩሲያና ኢራን በምርጫ ላይ ተፅዕኖ ማሳደር የሚያስችል ስራ ሲያከናውኑ ነበር ሲል አመላክቷል።

ከሩሲያ መንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት በጆ ባይደን ላይ ያልተረጋገጡ ክሶች ሲያቀርቡ እንደነበርና ምርጫውን ዝቅ ለማድረግና ለማጣጣል ዘመቻዎችን ሲያካሂዱ ነበር ተብሏል።

በሌላ በኩል ኢራን ከሩሲያ ተቃራኒ በተለያዩ መንገዶች የዶናልድ ትራምፕን ተፅዕኖ ለመቀነስ የተለያዩ ዘመቻዎችን ስታካሂድ እንደነበርም ሪፖርቱ ማመልከቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version