Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በምስራቅ ጎጃም ዞን የ20 ቀን ህፃንን ጨምሮ እናትና ሶስት ልጆቿ በእሳት አደጋ ህይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ ጎፍጭማ ቀበሌ የ20 ቀን ህፃንን ጨምሮ እናትና ሶስት ልጆቿ በእሳት አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

የእሳት አደጋው ወይዘሮ ሰገድ ይቴ በተባሉ እናት መኖሪያ ቤት በትናንትናው ዕለት ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 አካባቢ ለጊዜው መንስኤው ባልታወቀ ድንገተኛ ምክንያት የደረሰ ነው ተብሏል፡፡

የእሳት አደጋው ሲከሰት ቤት ውስጥ ያሉ ልጆቻቸውን ለማውጣት ወደ ቤት የገቡት ሟች ወይዘሮ ሰገድ ይቴ ሁለት ልጆችን አውጥተው ሶስተኛውን እና ከተወለደ 20 ቀን የሚሆነውን ህፃን ከተኛበት ለማንሳት ተመልሰው ወደቤት ሲገቡ የውጡት ሁለት ልጆቻቸው ተከትለዋቸው በመግባታቸው ተመልሰው ሳይወጡ ህይወታቸው ሊያልፍ መቻሉን የምስራቅ ጎጃም ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

Exit mobile version