Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አምባሳደር ነቢል ማህዲ የሹመት ደብዳቤያቸው ለደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት  ሳልቫ ኪር ማያርዲት አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ሱዳን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መንግስት ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ነቢል ማህዲ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት አቀረቡ።

ባለሙሉ ስልጣኑ አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን በዛሬው ዕለት ነው ለፕሬዚዳንቱ ያቀረቡት

በዚህ ወቅት  አምባሳደሩ የፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴን መልዕክት ለፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር ያቀረቡ ሲሆን፣ መልካም የሆነውን የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር እንደሚሰሩ ፕሬዚደንቱ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርም ኢትዮጵያ ለሀገራቸው ነጻነት ያበረከተችውን ድጋፍ በማስታወስ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር ለሚያደርጉት የስራ እንቅስቃሴ የመንግስታቸው ሙሉ ድጋፍ እንደማይለያቸው ማረጋገጣቸውን ከኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

Exit mobile version