Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል የማር ምርት ኢኒሼቲቭ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ‘ክልሉን የማር ባህር እናደርጋለን’ በሚል የማር ምርት ኢኒሼቲቭ ተጀመረ።
በጂማ ከተማ እየተካሄደ ባለው መርሃ ግብር የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የተለያዩ ዞኖች አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ወረዳዎች የተወጣጡ አርሷደሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የፕሮጀክቱ ሀሳብ አመንጪ የሆኑት አቶ ሽመልስ መንግስት በቡና እና ቅመማ ቅመም እንዲሁም የስንዴ መስኖ ልማት ኢኒሼቲቭን ጨምሮ በ15 ኢኒሼቲቮች ረገድ እየተሰሩ ያሉት ስራዎች የድህነት ታሪካችንን የመፋቅ አቅም አለው ብለዋል።
የማር ምርት በማሳደግ ፈጥነን እሴት በመጨመር አርሷደሮቻችን በቀላሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑም መንግስት ይሰራል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ።
ኢኒሼቲቩን ተግባራዊ ለማድረግም ክልሉ የዘመናዊ ቀፎ ዋጋ በ50 በመቶ ቅናሽ ተደርጎበት ለአርሷደሩ እንዲደርስ እየተደረገ ነው ብለዋል።
እስካሁንም ከ1 ሺህ 100 በላይ አርሳደሮች ተጠቃሚ ሆነዋል ነው የተባለው።
ኢኒሼቲቩ የአካባቢ ጥበቃ ላይ ካለው ፋይዳ በተጓዳኝ ለ24 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል እንደሚፈጥር እና የክልሉን ምርት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊየን ኪሎ ግራም ወደ 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ኪሎ ግራም ያሳድገዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በአፈወርቅ አለሙ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version