አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሃገራት ለመጡ ስደተኞች የኮቪድ19 ክትባት መስጠት ጀመረች፡፡
ክትባቱ በጋምቤላ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ስደተኞች መሰጠት መጀመሩን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡
እስካሁን የአስትራዜኒካ ኮቪድ19 ክትባት ለ405 ስደተኞች የተሰጠ ሲሆን፥ በስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ሰራተኞችም ክትባቱ መሰጠቱን ገልጿል፡፡
ክትባቱ የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት በትብብር የተሰጠ ነው ተብሏል፡፡
ኤጀንሲው ሁለተኛው ዙር ክትባት በሶስት ወራት ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቅሶ፥ ክትባቱ ለሁሉም ተደራሽ ይሆን ዘንድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!