Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮ ኩባ አደባባይ ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤከከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት ጋር በኢትዮ ኩባ አደባባይ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ከመስቀል አደባባይ እስከ ማዘጋጃ ቤት በሚሰራው ሞተር አልባ የእግረኛ መንገድ ማስዋቢያ ፕሮጀክት ላይ በሚገኘው ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ነው፡፡

መንገዱ ብዙ ታሪካዊ እና ማህበራዊ ቅርሶች የሚገኙበት እንደመሆኑ የማስዋብ ፕሮጀክቱ ለከተማዋ ውበት ለነዋሪዎች ደግሞ የመንፈስ እርካታ እና ጤንነት ትልቅ ትርጉም እንዳለው ወይዘሮ አዳነች ተናግረዋል፡፡

ለከተማዋ ውበት እና ለእንቅስቃሴ አመቺ የሆኑ የመንገድ አካፋይና ዳርቻን የማስዋብ ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ነው የተናገሩት ።

በተለይ ከማዘጋጃ ቤት-የአድዋ 00 ኪሎሜትር ጀምሮ እስከ መስቀል አደባባይ ድረስ እየተሰራ ያለው ፕሮጀክት ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ እየተሰራ ሲሆን፥ ለእግረኛ ፣ ለብስክሌት እና ለሌሎች አገልግሎቶች ምቹ ለማድረግ በመንገዱ አካፋይና ዳርቻ ላይ የችግኝ መትከል መርሐግብር መካሄዱን አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version