አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው የኩምሩክ የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ በይፋ ተጀምሯል፡፡
ግንባታውን የማአድንና ነዳጅ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በጋራ አስጀምረውታል።
ፋብሪካው ስራ ሲጀምር በአመት 7 ሺህ 500 ኪሎ ግራም ወርቅ የሚያመርት ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ 355 ሚሊየን ዶላር ወጪ ይደረግበታል ተብሏል፡፡
ፕሮጀክቱ በሚከናወንበት አካባቢ ከፍተኛ የወርቅ ምርት እንዳለ በጥናትና በናሙና በመረጋገጡ ፕሮጀክቱ ሌሎች ቀጣይ ክፍሎች የሚኖሩት ይሆናል።
የወርቅ ማምረቻው በአንድ ዓመት ጊዜ ተጠናቆ ወደ ምርት የሚገባ ሲሆን፤ ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ ማምረቻው ወደ ስራ ሲገባም ከ750 በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድልን እንደሚፈጥር ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በአጠቃላይ ማምረቻው ወደ ስራ ሲገባም በአመት የሚያመርተው 7 ቶን የወርቅ ምርት የሀገሪቱን የወርቅ ማምረት አቅምና የውጪ ምንዛሪ ገቢውን በከፍተኛ መጠን የሚያሳድገው ይሆናልም ተብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

