አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዦችን የምርመራና የክትባት መረጃ የሚይዝ መተግባሪያ በመጠቀም በአፍሪካ የመጀመሪያው ሆነ።
አየር መንገዱ የአለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ጉዞ ማለፊያ የሆነውን የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም ከአህጉሪቱ ቀዳሚ መሆን ችሏል።
የዚህ መተግበሪያ ሙከራም ከዛሬ ጀምሮ ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን እና ቶሮንቶ በሚደረጉ በረራዎች እና ከለንዶን እና ቶሮንቶ ወደ አዲስ አበባ በሚደረጉ በረራዎች ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑ ተጠቁሟል።
የሞባይል መተግበሪያው የተጎዦችን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እና የክትባት ሂደትን ለማረጋገጥ የሚስችል እና የሚያሻሽል ነው ተብሏል።
መተግበሪያው ለመንገደኞች ከጉዞ በፊት ምን አይነት ምርመራ ፣ ክትባት እና ሌሎች እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚገባቸው መረጃ ይሰጣል።
እንዲሁም ምርመራውን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ እና መንገደኞቹ በተረጋገጠ ፣ ደህንነቱ እና የግል በተጠበቀ መንገድ የምርመራ እና የክትባት ውጤት ለሚጠይቃቸው አካል እንዲሰጡ ያስችላል መባሉን ወርልድ ኤር ዌይን ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡