Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ህዝባዊ ተሳትፎ እና የግንባታ ሂደት የሚዘክር ሙዚየም ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ህዝባዊ ተሳትፎ እና የግንባታ ሂደት የሚዘክር ሙዚየም በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው፡፡
ሙዚየሙ ቤተመጻሕፍትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የዝክር ተቋማትን እንደሚያካትት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት እና የሚዲያ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሃይሉ አብርሃም ተናግረዋል።
ለአብነትም በከተማዋ የህዳሴ ግድብ ግዙፍ ፓርክ ለመገንባት የካርታ ርክክቡ ተጠናቆ የዲዛይን ስራው በሂደት ላይ እንደሚገኝ አቶ ሃይሉ ገልፀዋል።
ግድቡ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ አስተባባሪ ጽህፈት ቤቱም ሚናውን ስለሚያጠናቅቅ በቀጣይ ትኩረቱን ታሪክ መሰነድ ላይ አድርጎ ስራውን እንደሚቀጥል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
የግድቡ ግንባታ ከ2 ዓመታት በኋላ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version