አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ዶላር እናባዛለን በማለት የማጭበርበር ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡
ግለሰቦቹ ካሜሮናዊና ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ፥ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ሲ ኤም ሲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ሰዓት ዶላር እናባዛለን በማለት ለማጭበርበሪያ የሚጠቀሙባቸው ሁለት ካርቶን የጠቆረ ዶላር መሳይ ወረቀትና ሁለት ጠርሙስ ኬሚካል ይዘው መገኘታቸው ታውቋል፡፡
ከማህበረሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ኢንተለጀንስ ሁለቱንም ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን፥ በአሁኑ ሰዓት በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
እንደነዚህ አይነት ህገ-ወጥ ተግባር በሚፈጽሙ ግለሰቦች ዙሪያ ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!