አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሀላባ ባህል ማዕከል ለመገንባት የቦታ ርክክብ ተደረገ፡፡
በርክክቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው እንዲሁም በአዲስ አበባ እና አካባቢው የሚኖሩ የሀላባ ተወላጆች ተገኝተዋል።
በዚሁ ወቅት ወይዘሮ አዳነች “ኢትዮጵያውያን አንድነታችንን በማጠናከር የሁላችንንም ማንነት ማሳየት ይገባናል” ብለዋል።
የሀላባ ባህል ማዕከል ግንባታም በአዲስ አበባ የብሄረሰቡን ማንነት ለማሳየት የሚያስችል ይሆናል ብለዋል።
ዶክተር ሂሩት ካሳው በበኩላቸው ኢትዮጵያ በውስጧ በርካታ የባህል ትሩፋቶች ያሏት ሀገር እንደሆነች መጥቀሳቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር መሀመድ ኑርዬ በበኩላቸው በአዲስ አበባ የሀላባ ባህል ማዕከል ለመገንባት የቦታ ርክክብ መደረጉ እንዳስደሰታቸው ገልፀው ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

