አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት የዓይን ህክምና መስጫ ቁሳቁስ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ድጋፍ ተደረገ፡፡
ድጋፉን ያደረገው ባዮ ኢኮኖሚክ አፍሪካ የተባለ የበጎ አድራጎት ማህበር ነው፡፡
የማህበሩ መስራች ዶክተር ሰላም አሰፋ በመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በመገኘት ድጋፉን አስረክበዋል፡፡
በዚህ ወቅትም በማህበሩ የሚገኙ የዓይን ህመምተኞች ለህክምና ወደ መንግስት የህክምና ተቋማት በመሄድ አገልግሎቱን እንደሚያገኙ ጠቅሰው አሁን ግን እዚሁ ሕክምናው ሊሰጥ በመሆኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
በሃገሪቱ በርካታ ሃገር በቀል ማህበራት እንዳሉ ያነሱት ዶክተር ሰላም ሃገርና ህዝብን የሚጠቅም ስራ ለይተው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ዊንታ ቢሆነኝ በተቋሙ ብዙ አረጋውያን እንዳሉ አንስተው እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ ዓይናቸው የበለጠ ስለሚታመም ህክምናው እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል፡፡
ለተደረገላቸው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በፈትያ አብደላ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

