Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በትግራይ ክልል ከዛሬ ጀምሮ የኮሌራ ክትባት ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ከዛሬ ጀምሮ የኮሌራ ክትባት መሰጠት ሊጀምር መሆኑ ተገለፀ፡፡
በክትባቱ ከ2 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተደራሽ የሚሆኑ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል ተብሏል፡፡
ክትባቱ በዓለም የጤና ድርጅት እና በክልሉ ጤና ቢሮ ትብብር እንደሚሰጥ ከትግራይ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዓለም የጤና ድርጅት የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አስተባባሪ ዶክተር አባዲ ልኡል ክትባቱ በሁለት ዙር ከአንድ አመት በላይ ለሆኑ የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ክትባቱ ከኮሮና ቫይረስ ክትባት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው በመግለፅ ማህበረሰቡ እንዲከተብም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version