Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሰንበቴ ከተማ የሰላምና የእርቅ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰንበቴ ከተማ የሰላምና የእርቅ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
መድረኩ ባለፉት ጊዜያት በአጣዬ እና አካባቢው ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት ተከትሎ የተመለሰውን ሰላም ለማስቀጠል ያለመ ነው።
በሰላምና እርቅ መድረኩ ላይ የተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎች የሰላም ባለቤት ራሱ ማህበረሰቡ በመሆኑ ለዘላቂ ሰላም ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
የፖለቲካ ቁማርተኞች በጠነሰሱት ሴራ አላስፈላጊ ችግርና ቀውስ መድረሱን ያነሱት ነዋሪዎቹ፥ ጥፋተኞችን በጋራ ለማጋለጥ እንሰራለንም ነው ያሉት።
የመድርኩ ተሳታፊ የሃገር ሽማግሌዎች በበኩላቸው የአካባቢው ህዝብ ጥብቅ ትስስር ያለውና የማይለያይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“አባቶችና እናቶች ያስረከቡንን የመልካም ጉርብትናና ወንድማማችነት መንገድ ማስቀጠል ይገባልም” ነው ያሉት።
ያለ ሃገር ሰላም ሁሉም ነገር ከንቱ ነው ያሉት የመድረኩ ተሳታፊዎች ስለ ሰላም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም ሃሳባቸውን አካፍለዋል።
በእውነተኛ ይቅርታ እና ወንድማማችነት የሰላም ምሳሌ መሆን እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የዛሬው የእርቅና የሰላም መድረክ በአካባቢው ከዚህ ቀደም ሲደረግ ከነበረው የቀጠለ እንደሆነ ተመላክቷል።
በአወል አበራ እና ይስማው አደራው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version