አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻሸመኔ ከተማ በ5 ሚሊየን ብር የተደራጀው የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ (አይ ሲ ቲ) ማዕከል ተመረቀ፡፡
ማእከሉ 25 ኮምፒዩተሮች ያሉትና ኮምፒዩተሮቹም የመፅሐፍት መረጃ ክምችት ያላቸው መሆኑን ተነግሯል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ልጃለም አየለ ማእከሉ ወጣቱን ከቴክኖሎጂ ጋር ለማስተዋወቅ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።
አምስት መሰል ማዕከላት በክልሉ እየተገነቡ መሆኑን የገለፁት ዶክተር ልጃለም አየለ አጠቃላይ 40 ሚሊየን ብር ወጪ እንደተደረገባቸውም ነው የተናገሩት።
በተጨማሪም በዛሬው ዕለት የህዝብ የሚገለገልበት የጋራ መድሐኒት ቤት ጤና ጣቢያና የህዝብ መፀዳጃና የኮብልስቶን መንገዶች ተመርቀዋል።
በምርቃቱ ላይ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አበራ ወርቁና የክልሉ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ጀሚላ ሲንብሩ ተገኝተዋል።
በአጠቃላ በከተማው በ716 ሚሊየን ብር እየተሰሩ ካሉት 70 ፕሮጀክቶች መካከል 30 የሚሆኑትን በማስመረቅ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።
በጥላሁን ይልማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

