አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ጋር ተወያዮ፡፡
በዚህ ወቅትም ስደተኞችን ከመጠበቅ ፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን እና ለስደተኞች እየተሰጠ ስለሚገኘው የኮቪድ 19 ምላሽን በተመለከተ ውይይት ማድረጋቸውን አምባሳደሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
አምባሳደር ታዬ ለከፍተኛ ኮሚሽነሩ፤ ኢትዮጵያ የስደተኞችን ደህንነት ለመጠበቅና ለመከላከል ለረጂም ጊዜ የሚዘልቅ ዝግጁነት እንዳላት ገልፀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

