Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሐረማያ ሀይቅ ላይ ተደራጅተው ለሚሠሩ ወጣቶች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት ዳግም በተመለሰው የሐረማያ ሀይቅ ላይ በቡድን ተደራጅተው አሣ በማጥመድ ስራ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች ለአሣ ምርት የሚያገለግሉ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በድጋፍ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል የሱፍ፥ ስራው ጅማሮ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወደ ፊትም በሀይቁ ዙሪያ ጥናቶችና ልማታዊ ስራዎችን በቅንጅት ለመስራት መታቀዱንም ገልፀዋል፡፡

ጉዳዩ የዩኒቨርሲቲውን ብቻ ሳይሆን የሁሉንም አካል ያላሠለሠ ጥረት የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡

በከድር ሸምሰዲን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version