አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፀጥታ ሀይሎች ጎን በመቆም የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ ላይ መሆናቸውን የአዳማ ከተማ እና የምስራቅ ሸዋ ዞን ወጣቶች ተናገሩ።
ወጣቶቹ የምርጫው ሂደት ፍትሃዊና ሰላማዊ እንዲሁም ኢትዮጵያ የምታሸንፍበት እንዲሆን ሀላፊነታቸውን በመወጣት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በከተማዋና በዞኑ ገጠራማ ቀበሌዎች ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም የድምፅ መስጫ ወረቀታቸውን በአግባቡ በማስቀመጥ የምርጫውን ቀን እየጠበቁ መሆናቸውን አስረድተዋል።
የምርጫው ሂደት በሰላም እንዲጠናቀቅ በንቃት አካባቢያቸውን በመጠበቅ ላይ መሆናቸውንም ነው የገለፁት።
ከምርጫ ቦርድ ምስራቅ ሸዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ባገኘነው መረጃ ከ70 በመቶ በላይ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ቁሳቁስ የደረሰ ሲሆን፥ በቀሪዎቹ ለማድረስም እየተሰራ ነው።
ፋና ባደረገው ቅኝት የምርጫ ቁሳቁስ እየተጓጓዘ መሆኑንና ለምርጫው መሰናዶ የተለያዩ ድንኳኖች መተከላቸውን ተመልክቷል።
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!