Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የ8 ወር ነፍሰ ጡር የሆኑት እናት ድምፅ ሰጡ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ8 ወር ነፍሰ ጡር የሆኑት እናት በሃዋሳ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሜሪ ጆይ ቁጥር አንድ የምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፅ ሰጥተዋል፡፡

የምርጫ ካርዳቸውን ከወሰዱ በኋላ ጭንቀታቸው ምርጫውን እንዴት መሳተፍ እችል ይሆን የሚል እንደነበርና ይህም እንደተሳካላቸው ተናግረዋል፡፡

ልጃቸውን ለማቀፍ የተወሰኑ ቀናቶች የቀራቸው እናት ዜጎች በምርጫ ጣቢያቸው በመገኘት ድምፅ እንዲሰጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በብርሃኑ በጋሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version