አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ጎንደር ዞን በ1ሺህ 472 የምርጫ ጣቢያዎች የተካሄደው የድምፅ ቆጠራ ሂደት መጠናቀቁን በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ጎንደር ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ አምሳሉ በለጠ በሰጡን መግለጫ በሁሉም ጣቢያዎች የተቆጠሩ ድምፆች ወደየማዕከላት እየተሰበሰቡ ነው።
የድምፅ ቆጠራ ሂደቱ ሁሉም ተወካዮች በተገኙበት እንደተከናወነ የተናገሩት አቶ አምሳሉ፥ አጠቃላይ የተመዘገበው ህዝብና የተሰጠው ድምፅ ሁሉም ጣቢያዎች አስረክበው እንደጨረሱ ተጠቃሎ የሚገለፅ ይሆናል ብለዋል።
በሙሉጌታ ደሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!