አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ጨምሮ ዘጠኝ ሀገራት የተካተቱበት የናይል ኢኳቶሪያል ሐይቆች የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡
ለአንድ ዓመት ያህል ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት ስትመራው የቆየችው የቀጠናው የልማት ትብብር ሀገራቱን የሚያስተሳስሩ የተለያዩ የኢነርጂ ስራዎችን እንዳከናወነ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ ተናግረዋል።
በቀጠናው የድህነት ቅነሳ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል በሀገራቱ መካከል በትብብር እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።
ቀጠናው በተፈጥሮ ሀብት የታደለ ቢሆንም በትብብር ከመስራት አንፃር ብዙም እንዳልተጓዘ የሱዳን የመስኖና የውሃ ሃብት ሚኒስትር ያሲር መሀመድ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

