Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሰላም ባህሪ እንደ ህፃን ልጅ ሁሌም ክትትል ይፈልጋል – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሰላም ባህሪ እንደ ህፃን ልጅ ሁሌም ክትትል ይፈልጋል ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለፁ፡፡
ይህ የተባለው የሲዳማ ክልል ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ሽልማት በሰጡበት ነዉ።
ያለን ህዝብ ሰላም ወዳድ ሆኖ ፖለቲከኞች ለራሳቸዉ ፍላጎት የሚያለያዩት ነዉ ያሉት አቶ ደስታ ፖለቲከኞቹ በመቀራረብ አንድነቱን ማጠናከር እንደሚጠበቅባቸው ገልፀል፡፡
ለሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ሰላምን የማስጠበቅ ሂደት ላይ ላሳዪት ትልቅ አስተዋፅኦ የወርቅ ሜዳሊያ ተበርክቶላቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሽልማቱን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ያዘጋጀው ሲሆን÷ የክልሉ አጎራባች ዞኖች አመራሮች፣ ደቡብ እዝ ፣ ፌደራል ፖሊስና የክልሉ ሚሊሻና ልዩ ሀይል እንዲሁም ተቋማት የሜዳሊያ፣ የዋንጫና የሰርተፍኬት አበርክቶ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እጅ ተቀብለዋል፡፡
በመቅደስ አስፋው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version