Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጉምሩክ ኮሚሽን ከአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽንና የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታና የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሃና ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ የኢትዮጵያን የወጪና የገቢ ንግድ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ፣ቀልጣፋና ፍትሀዊ እንዲሁም በእውቀት ላይ ተመስርቶ እንዲመራ ለማስቻል እስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን አቶ ደበሌ ቃበታ ገልፀዋል፡፡
ፕሮፌሰር ጣሰው በበኩላቸው ÷ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በሰው ሀይል ልማት ፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም የጉምሩክ አሰራርን ይበልጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ የሚያደርጉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለመፍጠር ይበልጥ ተቀራርቦ ለመስራት እንደሚያግዝ ገልፀዋል፡፡
ኮሚሽኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆንና የወጪና የገቢ ንግዱ ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሆንም ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ፕሬዚዳንቱ መግለፃቸውን ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም ኮሚሽኑ ቅርሶች በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር እንዳይወጡና ወደ ሀገር እንዳይገቡ ከኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ጋር፣ የወጪና የገቢ ንግድ እቃዎች እንቅስቃሴ ይበልጥ ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን ከኢትዮጵያ ጉምሩክ አስተላላፊዎች የሙያ ማህበር ጋር እንዲሁም በኢትዮጵያ ጤናማ የንግድ ስርዓት እንዲሰፍን ከኢትዮጵያ ሴቶች ላኪዎች ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version