Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ147 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 58 ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን ኦሞ ቤየም ወረዳ ከ147 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 58 ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።
በወረዳው ባለፉት ዓመታት 78 ፕሮጀክቶችን ከ193 ሚሊየን ብር በላይ በጀት ለመስራት ታቅዶ በዛሬው ዕለት በ147 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ግንባታቸው የተጠናቀቀ 58 የተለያዩ ፕሮጀክቶች የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል።
የተመረቁት ፕሮጀክት 90 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የጠጠር መንገድ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣የወረዳው አስተዳደር ህንፃ ጨምሮ የተለያዩ ፅህፈት ቤቶች ህንፃዎች ናቸው።
በ2009 ዓ.ም በአዲስ ወረዳነት ስትመሰረት ከፍተኛ የሆነ የመሰረተ ልማት ችግር እንደነበር የተናገሩት የኦሞ ቤየም አስተዳዳሪ አቶ መሐመድአሚን ሼ ከሊፋ ባለፉት ሦስት ዓመታት የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለሚቀርፉ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ በመስጠት ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ አድርገናል ብለዋል።
የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱል ሃኪም ሙሉ በበኩላቸው÷ እንደ ዞን የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶች በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በማድረግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ከመቅረፍ ባሻገር ህዝባዊ ወገንተኝነታችንን ያሳያል ሲሉ ገልፀዋል።
በዚሁ የምርቃት ዝግጅት ላይ በግብርና ሳይንስ ስልጠና የወሰዱ 323 ግንባር ቀደም አርሶ አደሮችም ተመርቀዋል።
በተመስገን አለባቸው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
Exit mobile version