አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ መልከፀዴቅ እና ሌሎች የሀይማኖት አባቶች በተገኙበት የቤት እድሳቱን አስጀምረዋል።
በጎ ማድረግ ከፈጣሪ የተማርነው ተግባር ነው ያሉት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ መልከፀዴቅ ሁሉም በሚችለው አቅሙ ያለውን በማካፈል ሊተጋገዝ እና ሊረዳዳ ይገባል ብለዋል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ ከመንፈሳዊ ግልጋሎት ባለፈ በማህበራዊ አገልግሎቶች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ የልማት ስራዎች በመሳተፍ የምታደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክራ እንደምትቀጥል ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ መልከፀዴቅ ገልጸዋል።
የቤት ዕድሳት ከሚደረግላቸው ነዋሪዎች መካከል ምንም ደጋፊ ለሌላቸው አንዲት እናት ብጹዕ አቡነ መልከፀዴቅ በግላቸው ለአንድ ዓመት ወጪ የሚሆን የ24 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባለፈው ሳምንት በይፋ በተጀመረው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 12 የአቅመ ደካማ ነዋሪ ቤቶችን እድሳት ለማድረግ ቃል መግባቷ ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

