አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ “በልጆች ልብ ችግኝ እንትከል”በሚል ከከተማው ከተውጣጡ ከ1 ሺህ ህጻናት ጋር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ።
ከህጻናቱ ጋር ችግኝ የተከሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፥ “ዛሬ ከህፃናት ጋር ችግኝ የምንተክለው በህፃናት ልብ ላይ መልካም ዘር ለመዝራት ነው” ብለዋል፡፡
ይህም መልካም ዜጋንና ምቹ ሀገርን ለመገንባት ወሳኝነት እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡
ህጻናት ዛሬ የተከሉት ችግኝ ፍሬ እንዲያፈራ መንከባከብ እና መጠበቅ አለባቸው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፥ ህጻናቱ ከወዲሁ የስራ እና የትጋት ልምምድ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ገልጸዋል፡፡
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ተክሌ በበኩላቸው የነገዋን ኢትዮጵያ የሚረከቡ ህፃናት የተገነባች ሀገር መረከብ ብቻ ሳይሆን ሀገር በመገንባት ሂደትም የበኩላቸውን አሻራ እንዲያኖሩ ለማድረግ የወላጆች ጥረት ሊታከልበት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
“ኑ አዲስ አበባን እናልብስ” በሚል በዘንድሮ የክረምት ወራት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብር በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል በእቅድ መያዙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመላክታል ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

